ቀጥታ፡

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

ሀረር፤ ሐምሌ 9/2018(ኢዜአ)፡- የሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ እያካሄደ ያለው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነው።
 
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የምክር ቤቱ ጉባኤ የ2018  በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።


 

ለጉባዔው በቀረበው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የምክር ቤቱ አባላት ከተወያዩበት በኋላ ያፀድቁታል ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉ ምክር ቤት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።


 

ምክር ቤቱ የሚቀርቡለትን የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶንች ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም