ቀጥታ፡

አርጀንቲና እንግሊዝን በመርታት ለፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር አርጀንቲና ከመመራት ተነስታ እንግሊዝን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ማምሻውን በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የ25 ዓመቱ የክንፍ መስመር ተጫዋች አንቶኒ ጎርደን በ55ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል እንግሊዝን መሪ አድርጓል።

ሞርጋን ሮጀርስ ኳሷን አመቻችቶ አቀብሏል።

አርጀንቲና ከግቡ መቆጠር በኋላ ተጭና ተጫውታለች።

ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ85ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል አርጀንቲናን አቻ አድርጓል።

ላውታሮ ማርቲኔዝ በ92ኛው ደቂቃ የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

እንግሊዝ መሪነቷን ማስጠበቅ አልቻለችም።

ጨዋታው ጉልበት እና ኃይል የተቀላቀለበት ነበር። በርካታ ጥፋቶችም ተሰርተዋል።

ሊዮኔል ሜሲ ለ12ኛ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ለግብ የሚሆን ኳስ በማቀበል አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ስምንት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ አርጀንቲና ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አልፋለች።

የወቅቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ አርጀንቲና ለስድስተኛ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ደርሰዋል።

አርጀንቲና በፍጻሜው ከስፔን ጋር ትገናኛለች።

እንግሊዝ ለሁለተኛ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ የማለፍ ህልሟ አልተሳካም።

እንግሊዝ ከፈረንሳይ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይጫወታሉ።

ስፔን ከአርጀንቲና ዋንጫውን ለማንሳት እሁድ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም ይፋለማሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም