ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን ለነገ እንድትሆን ሆና ልትገነባ ተሰባስባለች-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን ለነገ እንድትሆን ሆና ልትገነባ ተሰባስባለች-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን ለነገ እንድትሆን ሆና ልትገነባ ተሰባስባለች ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ልሂቃን በሚፈጥሩት ግጭት ሕዝባችን ቢታመስም ባህላችን ግን ለምክክር ያደላ ነበር ብለዋል፡፡
ቤታችን፣ ሞሰባችን፣ አቀማመጣችን፣ ማብሰያችን፣ ወዘተ ክብ ናቸው።
ይሄውም ነገርን ሰብሰብ ብሎ በመመካከር ለመከወን እንዲያመች የተሠራ ነው። ክብ መነሻና መድረሻ የለውም። ሩቅና ቅርብ የለውም። ወጪና ገቢ የለውም። ሁሉንም በእኩልነት ያሳትፋል ሲሉ ገልፀዋል።
ይሄንን የተረሳ ባህላችንን ወደ ሀገራዊ ምክክር አምጥተነዋል። ኢትዮጵያውያን ከአራቱም ማዕዘን መጥተው በጋራ ይመክራሉ። እሺ በጄ ያለ ሁሉ ዕድል ተሰጥቶታል። እነሆ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን ለነገ እንድትሆን ሆና ልትገነባ ተሰባስባለች ብለዋል ።
የሀገር ጸሎት ልብና ጆሮ ከእናንተ ጋራ ነው ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።