ቀጥታ፡

ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በእጅጉ የገዘፈ ዓላማ እና ተግባር ያለው ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ በቀላሉ የማይደገም በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ እጅግ የገዘፈ ዓላማና ተግባር ያለው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ጉባኤው በቀላሉ የማይደገም፣ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በእጅጉ የገዘፈ ዓላማ እና ተግባር ያለው ነው።

ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር መድረክ ለአፍሪካ በብዙ ምሳሌ የሚሆን ሁሉን አቀፍ መድረክ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መድረኩ ልባም ለሆኑ ሰዎች ትልቅ ዕድል መሆኑን ጠቁመው፤ ይህ መድረክ በታላቅ አክብሮት መከናወን እንደሚገባው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን ብዙ መከራዎችን አሳልፈዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ምክክር ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

መጪው ትውልድ ዘመኑ እንዲያምር ምክክሩ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው፤ ይህንን መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል።

ምክክሩ እንደ ታላቅ ዕድል እና መሠረት የሚታይ መሆኑን ጠቁመው፤ የተፈጠረውን ዕድል ለመጠቀም የምንተጋ መሆን አለብን ብለዋል።

ተመካካሪዎች ለኢትዮጵያ መምከር እንዳለባቸው ገልጸው፤ መልካም መሠረት ማኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመደማመጥና በመተማመን ላይ መገንባት እንደሚገባም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም