የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ ሰላም እንድታጸናና ሀገር በቀል ሰላማዊ መፍትሄዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ ሰላም እንድታጸናና ሀገር በቀል ሰላማዊ መፍትሄዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላል
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ ሰላም እንድታጸናና ሀገር በቀል ሰላማዊ መፍትሄዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችል የአፍሪካ ህብረት ገለጸ።
የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ሀገር በቀል ሰላማዊ አማራጮችንና የምክክር ሂደትን መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መክፈቻ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር እየተካሄደ ይገኛል።
የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ይህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ ሰላም እንድታጸናና ሀገር በቀል ሰላማዊ መፍትሄዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ሀገር በቀል ሰላማዊ አማራጮችንና የምክክር ሂደትን መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ጅማሮ ታሪካዊ ቀን መሆኑን ጠቁመው የአፍሪካ ህብረት የዚህ ታሪካዊ ሁነት አካል በመሆኑ ኩራት እና ክብር እንደሚሰማው ገልጸዋል።
የሀገራዊ ምክክር ጥልቀቱን፣ አሳታፊነቱን፣ አካታችነቱንና ብዝሃነቱን እናደንቃለን ያሉት አምባሳደር ባንኮሌ የአፍሪካ ህብረት ይህን ታሪካዊ ሂደት እንደሚደግፍ አመልክተዋል።
ይህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ ሰላም እንድታጸናና ሀገር በቀል ሰላማዊ መፍትሄዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።
ምክክሩ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ሰላምና መረጋጋትን በዘላቂነት ለማስፋን ቁልፍ ሚና እንደሚጫወትም ነው የገለጹት።
እንደ አፍሪካ የኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋትና አንድነት ለቀጣናውና ለመላው አፍሪካ ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ከ63 ዓመታት በላይ በአዲስ አበባ መቀመጫውን በማድረጉ ክብር እንደሚሰማው ገልጸዋል።
አሁንም ሰላምን ለማረጋገጥ፣ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥ እንዲሁም የሁሉም ኢትዮጵያውያን ህልሞች ከአጀንዳ 2063 ጋር እንዲጣጣሙ ህብረቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።
በጋራ መግባባት እና መከባበር የሚካሄዱ ሂደቶች ሰላምን ለማምጣት ወሳኝ ሚና እንደሚወጡ ጠቁመዋል።