በአረንጓዴ አሻራው በመዲናዋ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን እየሰራን እንገኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
በአረንጓዴ አሻራው በመዲናዋ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን እየሰራን እንገኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7/2018 (ኢዜአ)፦ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች ዛሬ ከጽ/ቤታቸው አመራሮችና ሰራተኞች ጋር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በኤአይ( AI) ዩኒቨርሲቲ አካሂደዋል።
በዚህም በዘንድሮው ክረምት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማችን 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን እየሰራን እንገኛለን ነው ያሉት።
የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሰኔ 7/2018 ዓ.ም አስጀምረን እስካሁን 4 ሚሊዮን 469 ሺህ 710 ችግኞችን ተክለናል ብለዋል።
የችግኝ ተከላ አፈፃፀሙም 75 በመቶ ደርሷል ያሉ ሲሆን ችግኝ መትከል ብቻውን ከምናልመው ግብ ስለማያደርሰን የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራም እንሰራለን በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።