ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 7/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ዋዜማ፣ የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ ከሆኑት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን በመልዕክታቸው ላይ አስፍረዋል።
በመጪው ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ለመወያየት እንዲሁም ከዚህ ቀደም ካከናወኗቸው ተግባራት ጥበብ ለመቅሰም የተቻለ ሲሆን፤ በተለይም የቢያፍራን የሰላም ሂደት በመምራት ያካበቱትን ልምድ ማጋራታቸውን አመልክተዋል።
ይህም ኢትዮጵያ በምክክር ለምታረጋግጠው አንድነትና ዘላቂ የሰላም ጉዞ ላይ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ኦባሳንጆ ለሚያበረክቱት በዋጋ የማይተመን አስተዋጽኦ ሁልጊዜም የላቀ ምስጋናዋን ታቀርባለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።