ቀጥታ፡

የኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) በሉሳይል ቤተመንግስት ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) በሉሳይል ቤተመንግስት ተቀብለው አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ፣ በቀድሞው አሚር ሼክ ሃማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀድሞው አሚር ሼክ ሃማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ህልፈትን ተከትሎ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ የቀድሞው አሚር በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን፣ ለውይይትና ለድርድር መሠረት በመጣል ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ጥበበኛ መሪ እንደነበሩ መግለጻቸው ይታወሳል።

በተለይም ለኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት ይሰጡ እንደነበርና የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከመጀመሪያው ሒጅራ ጀምሮ የቆየ ጥልቅ ታሪካዊ መሠረት እንዳለውም እንዲሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀድሞው የኳታር አሚር ሼይኽ ሀማድ ቢን ካሊፋ አልታኒ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ለኳታር ሕዝብ እና መንግሥት ሐዘናቸውን ለመግለጽ ኳታር መግባታቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም