የአዲስ አበባ ከተማ የ2019 በጀት 502 ነጥብ 27 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ከተማ የ2019 በጀት 502 ነጥብ 27 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 502 ነጥብ 27 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ።
ከበጀት ድልድሉ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዘው የካፒታል በጀት ሲሆን፤ 71 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ ያለው እንደሆነ ተገልጿል።
እንዲሁም 25 ነጥብ 3 በመቶው ለመደበኛ ወጪ ተመድቧል።
በጀቱ የከተማዋን የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ የተመደበ ሲሆን፣ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል እንደሆነ ተመልክቷል።
በተጨማሪም ለማህበራዊ ልማት፣ ለውሃ አቅርቦትና ሁሉንም አቀፍ የልማት ሥራዎች በተሳለጠ መንገድ ለማቅረብ የሚያስችል በጀት መሆኑም ተገልጿል።
ከፍተኛ ድርሻ የያዘው የካፒታል በጀቱ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለቤት ልማት፣ ለመሠረተ ልማት ግንባታ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትን ማሻሻልና አጠቃላይ የከተማዋን ልማትና ዕድገት ይበልጥ ለማዘመን የተመደበ እንደሆነ ተገልጿል።