ቀጥታ፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ 6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ሐምሌ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በነገው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጣልያን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በፈረንሳይ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረጉ የብድር ስምምነቶችን ለማጽደቅ የሚቀርቡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም