ቀጥታ፡

አዲስ አበባ ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ምሳሌ የሚሆን አስደናቂ ዕድገት እያስመዘገበች ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/ 2018 (ኢዜአ):- አዲስ አበባ ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ምሳሌ የሚሆን አስደናቂ ዕድገት እያስመዘገበች መሆኗን የአፍሪካ ሕክምና ትምህርት ጉባዔ ተሳታፊዎች ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሕክምና ትምህርት ጉባኤ (MedEdAfrica 2026) ዛሬ ተጠናቋል።

የጉባዔው ተሳታፊዎች በከተማዋ የአድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን፥ በተመለከቱት ለውጥ በእጅጉ መደነቃቸውን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ምሳሌ የሚሆን አስደናቂ ዕድገት እያስመዘገበች እንደምትገኝም ተናግረዋል።

በቆይታቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ያደረጉላቸው ደማቅ እንግዳ ተቀባይነት እንዳስገረማቸው አንስተው፤ በሁለተኛ ቤታቸው ኢትዮጵያና በውቧ የአህጉሪቱ መዲና አዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ መደሰታቸውንና መኩራታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም