ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ የጋራ ፍላጎታቸውን መሠረት አድርገው በትብብር እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/ 2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ ሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር አብዱላህ ቢን ሀሰን አል-ዛህራኒ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።


 

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ ያላቸውን የረጅም ዘመን የሁለትዮሽ ግንኙነት አድንቀዋል።

ሁለቱ ወገኖች የጋራ ትኩረት በሆኑ ቀጣናዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም ሀገራቱ የጋራ ፍላጎታቸውን መነሻ በማድረግ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንዲሁም በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም