ከአገልግሎት ዘርፍ 9 ነጥብ 8 በመቶው ዕድገት ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
ከአገልግሎት ዘርፍ 9 ነጥብ 8 በመቶው ዕድገት ይጠበቃል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ የአገልግሎት ዘርፍ 9 ነጥብ 8 በመቶው ዕድገት እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው፤ የኢትዮጵያ የአገልግሎት ዘርፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እያደገ መምጣቱን አመላክተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በአዲስ አበባ ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች መካሔዳቸውን ጠቅሰው በነዚህ ስብሰባዎች ለሚሳተፉ አካላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰፊ የማጓጓዝ አገልግሎት መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡
የዓለም አቀፍ ስብሰባው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያገኙት ከሆቴሎች መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአገልግሎት ዘርፍ 9 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት እንደሚጠበቅም ጠቅሰው ዘርፉ ከፍተኛ የስራ እድል አማራጭ እየሆነ መምጣቱንም እንዲሁ፡፡