ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለውጡ በፊት ከነበረው መንገደኞችን የማጓጓዝ አቅም በለውጡ ዓመታት በሶስት እጥፍ አሳድጓል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለውጡ በፊት ከነበረው መንገደኞችን የማጓጓዝ አቅም በለውጡ ዓመታት በሶስት እጥፍ ማሳደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአገልግሎት ዘርፍ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገልግሎቱ አድማሱ እየሰፋ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለውጡ በፊት ከነበረው መንገደኞችን የማጓጓዝ አቅም በለውጡ ዓመታት በሶስት እጥፍ ማሳደግ እንደቻለ ተናግረዋል።

ለማሳያም የዚህ ዓመቱን ያነሱ ሲሆን በ2018 ዓ.ም አየር መንገዱ አጠቃላይ 21 ሚሊየን የውጭና የሀገር ውስጥ መንገደኞችን ማጓጓዙን ገልጸዋል።

ከላይ ከተጠቀሰው ቁጥር ውስጥ 17 ሚሊየን የሚሆኑት የውጭ ሀገራት ተጓዦችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማጓጓዝ እንደቻለ አብራርተዋል።

አየር መንገዱ በሰጠው አገልግሎትም ለኢትዮጵያ ሃብት እንድታገኝ አቅም መፍጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም