የትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ የትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ዘርፍ ጥራት እና ለውጦችን በተመለከተ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ የትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት ተማሪዎች በራሳቸው ተማምነው ፈተና የሚወስዱበት አሰራር መተግበሩን ጠቁመው በዚህም የኩራጃ ባህልን ማስረቀት ተችሏል ነው ያሉት።
ትምህርት ከታች ካልተሠራ ከላይ መሥራት ውጤታማ አያደርግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመዋዕለ ህጻናት ማስፋፊያ በተሰጠው ትኩረት 35 ሺህ መዋዕለ ሕጻናትን መገንባት ተችሏል ብለዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ኩረጃን ለማስቀረት፣ ትምህርትን በቴክኖሎጂ ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ሙከራ ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ደረጃቸውን የጠበቁ እጅግ አበረታች ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትምህርትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ።