የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በዘመናዊ መንገድ መቅረጽ እና ማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ ሆነዋል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በዘመናዊ መንገድ መቅረጽ እና ማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ ሆነዋል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ብልጽግና እና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በዘመናዊ መንገድ መቅረጽ እና ማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ የኢትዮጵያን ብልጽግና እና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በዘመናዊ መንገድ መቅረጽ እና ማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ወደ ተግባር ገብተዋል።
በዚህም ግብርናን በቴክኖሎጂ በማዘመንና ቱሪዝምን በማስፋፋት፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የውጭ ምንዛሬን ማሳደግ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመተግበር ስኬታማ መሆኑን ገልጸዋል።
የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር እና የግል ዘርፉን በማበረታታት መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት መቻሉንም ተናግርዋል።
ይህ የኢኮኖሚ ለውጥ የዓለም አቀፍ ጫናዎችን የመቋቋም፣ እንቅፋቶችን ወደ ዕድል የመቀየር እና የራስን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር መርሆዎችን በተግባር እያሳየ እንደሚገኝ ገልጸዋል።