ባንዳዎችንና ጽንፈኞችን የምናሸንፈው በተጠናከረ ውይይት ብቻ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ባንዳዎችንና ጽንፈኞችን የምናሸንፈው በተጠናከረ ውይይት ብቻ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ ባንዳዎችንና ጽንፈኞችን የምናሸንፈው በተጠናከረ ውይይት ብቻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላምና መረጋጋትን በተመለከት በሰጡት በምላሽ እና ማብራሪያ ባንዳዎችንና ጽንፈኞችን የምናሸንፈው በተጠናከረ ውይይት ብቻ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ አለመረጋጋቶችን ለመፍታት መንግሥት ከ4000 በላይ የምክክር መድረኮችንና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁን የብሔራዊ መግባባት ምእራፍ ተሻግረናል ሲሉ ገልጸዋል።
ባንዳዎችንና ጽንፈኞችን የምናሸንፈው በተጠናከረ ውይይት ብቻ ነው ሲሉም በምላሻቸው አክለዋል።