ቀጥታ፡

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ለውጥ እያመጣ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ሰኔ 30/2018 (ኢዜአ):-በትምህርት ዘርፉ ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ምላሽ እየሰጡ ይገኛል።

በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት አመታት ተማሪዎች በራሳቸው ተማምነው ፈተና የሚወስዱበት አሰራር መተግበሩን ገልጸው፤የኩራጃ ባህልን ማስረቀት እየተቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

በትምህርት መስክ በተሠራው ሥራ ከፍተኛ ስኬት ተመዝግቧል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለመዋዕለ ህጻናት ማስፋፊያ በተሰጠው ትኩረት 35 ሺህ መዋዕለ ሕጻናትን መገንባት ተችሏል ብለዋል።

ትምህርት ከታች ካልተሠራ ከላይ መሥራት ውጤታማ አያደርግም ሲሉም አክለዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ኩረጃን ለማስቀረት፣ ትምህርትን በቴክኖሎጂ ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ሙከራ ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት።

አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም እጅግ አበረታች ደረጃቸውን የጠበቁ ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም