የዘንድሮ ምርጫ ለየትኛውም የፖለቲካ አካል እጅግ አስተማሪና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥልቅ አሳቢነትና ሰላም ወዳድነት በትልቁ ያሳየ ትልቅ ታሪካዊ ሁነት ሆኖ ተመዝግቧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የዘንድሮ ምርጫ ለየትኛውም የፖለቲካ አካል እጅግ አስተማሪና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥልቅ አሳቢነትና ሰላም ወዳድነት በትልቁ ያሳየ ትልቅ ታሪካዊ ሁነት ሆኖ ተመዝግቧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ የዘንድሮ ምርጫ ለየትኛውም የፖለቲካ አካል እጅግ አስተማሪና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥልቅ አሳቢነትና ሰላም ወዳድነት በትልቁ ያሳየ ትልቅ ታሪካዊ ሁነት ሆኖ ተመዝግቧል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ምርጫውን በተመለከተ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
በምላሻቸውም የዘንድሮ ምርጫ ለየትኛውም የፖለቲካ አካል እጅግ አስተማሪና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥልቅ አሳቢነትና ሰላም ወዳድነት በትልቁ ያሳየ ትልቅ ታሪካዊ ሁነት ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋለ።
የዘንድሮ ምርጫ ከሌላው ጊዜ በተለየ ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞት ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በፊት እንደተለመደው ፍጥጫው በተፎካካሪዎች መሀል ብቻ እንዳልነበር ጠቁመው ይልቁንም እራሱ ምርጫው የተጠናከረ ጥቃት ኢላማ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
ነገር ግን ማሸነፍና ፈተና መሻገር እንዲሁም ሀገር በማጽናት ልምዳቸው የሚታወቁት ኢትዮጵያውያን ምርጫውን በማካሄድ ጽንፈኝነትን እና ዘረኝነትን አሻፈረኝ በማለት ከዳር እስከዳር ድምጻቸውን አስተጋብተዋል ነው ያሉት።
በተጨማሪም በአፍሪካና በዓለም የዲሞክራሲ ታሪክ መኖሩን በሚያጠራጥር ሁኔታ ብልጽግና ፓርቲ በ85 በመቶ መቀመጫ በመወዳደርና የተቀረውን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በመተው፤ ታላቅ የዲሞክራሲ ቀናዒነት የታየበት ምርጫ ነበር ብለዋል።