ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

ምርጫን በሚመለከት

👉 ለየትኛውም የፖለቲካ አካል ትምህርት የሰጠ ምርጫ ተካሂዷል።

👉 አትመዝገቡ፣ አትደግፉ፣ አትምረጡ የተባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማስፈራሪያዎችን ትቶ በንቃት በምርጫው ተሳትፏል።

👉 ምርጫ በማይወዱ አካላት ምርጫው ራሱ እንዳይከናወን የጥቃት ዒላማ ተደርጎ ነበር፤ ነገር ግን በስኬት ተጠናቋል።

👉 የኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው የተባበረ ክንድ ለሀገሩ መጻዒ ዕድል ላደረገው አበርክቶ ከፍተኛ ክብር ይገባዋል።

👉 ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ ለሀገራቸው የሚበጀውን አሳውቀዋል፤ ለሀገራቸው የማይበጀውን ደግሞ አልሰሙም።

👉 አዛውንቶች፣ የወለዱ እናቶች፣ በህመም ላይ ያሉ ሰዎች፣ ጥይት እየተተኮሰባቸው ብሎም ምቹ ባልሆኑ ሁኔታዎች ጭምር ሆነው ኢትዮጵያውያን በምርጫው በንቃት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም