የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል፦ - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል፦
✍️በኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝብ ጥያቄን ለመፍታት እና የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ የሚደነቅ ነው
✍️በኢትዮጵያ ዘላቂ የሰላም ግንባታን ከማጠናከር አንጻር ምን አቅጣጫ ተይዟል ?
✍️በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማቃለል መንግስት የያዘው አቅጣጫ ካለ ቢብራራ
✍️7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው
✍️የሀገርን ሰላም አና አንድነት ለማናጋት በባንዳነት ተግባራት ላይ የተሰለፉ አካላትን እንቅስቃሴ መንግስት እንዴት ይመለከታል ?
✍️በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ ለህዝብ የሚኖራቸው ፋይዳ ከፍተኛ ቢሆንም ከአካባቢው ለልማት የሚነሱ ዜጎች ጉዳይ እንዴት ይታያል ?
✍️መንግስት የከተማ ልማትን ለማሳደግ እየሰራቸው የሚገኙ ተግባራት ለሀገር ብልጽግና ከሚኖራቸው ፋይዳ ባሻገር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው
✍️የወጣቶች ስራ አጥነትን ጉዳይ በዘላቂነት ትኩረት ለመፍታት ምን ተይዟል?
✍️በከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ችግር ለማስተካከል የሚደረገውን ጥረት አስመልክቶ ማብራሪያ ቢሰጥ
✍️የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አግባብነት ያለው እና ለህዝባችን ዘላቂ የብልጽግና ጉዞ ወሳኝ ነው
✍️ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን አቅም ለማሳደግ እየተሰሩ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ናቸው
✍️በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበትን አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ምን አቅጣጫ ይዟል?
✍️ ሀገሪቱ የሚገባትን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ በተለይም በመንገዶች ማስፋፊያ እና ጥራት ማሻሻል ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል
✍️ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር መንግስት የሚከተለው አቅጣጫ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ
✍️ በጤናው ዘርፍ የሚታየውን የመድሀኒት እቅርቦት እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ ምን አይነት ተጨባጭ ርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል?
✍️መንግስት ከተሞችን ለዜጎች ምቹ እና ለቱሪዝም ተመራጭ ለማድረግ እየሰራቸው ያሉ ተግባራት የሚደነቁ ናቸው