ስፔን ፖርቹጋልን በማሸነፍ ወደ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ስፔን ፖርቹጋልን በማሸነፍ ወደ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/ 2018 (ኢዜአ):- በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የ 16ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ተጠባቂ ግብር ስፔን ፖርቹጋልን 1 ለ 0 ረትታለች።
ማምሻውን በዳላስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ሚኬል ሜሪኖ በ91ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ፌራን ቶሬስ ኳሱን አመቻችቶ አቀብሏል።
ተመጣጣኝ ፉክክር በታየበት ጨዋታ ስፔን የግብ እድሎችን በመፍጠር ተሽላ ተገኝታለች።
የ"አይቤሪያ ደርቢ" በስፔን አሸናፊነት ተጠናቋል።
ስፔን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ግብ ያልተቆጠረባት ብቸኛ ሀገር ናት።
ውጤቱን ተከትሎ ስፔን ወደ ሩብ ፍጻሜው የገባች አምስተኛ ሀገር ሆናለች።
በሩብ ፍጻሜው ከአሜሪካ እና ቤልጂየም አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
ስፔን የአንድ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ናት።
የክርስቲያኖ ሮናልዶዋ ፖርቹጋል የዓለም ዋንጫ ጉዞዋ 16 ውስጥ ተገቷል።
የ41 ዓመቱ ሮናልዶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን የማንሳት ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል። ተጫዋቹ ዘንድሮ የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ መሆኑን ከጨዋታው በፊት ገልጾ ነበር።
ሁለቱ ሀገራት ዓለም ዋንጫን ያሸንፋሉ ተብለው ግምት የተሰጣቸው ናቸው።
አሜሪካ ከቤልጂየም ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በሲያትል ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።