ቀጥታ፡

የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል።

በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያሳረፈችው የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር፤ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቿና በርካታ የሙያ አድናቂዎቿ በተገኙበት በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።


 

ከያኒዋ ካበረከተቻቸው በርካታ የሙዚቃ ሥራዎቿ መካከል "ኢትዮጵያ"፣ "አራዳ"፣ "እንደ ኢየሩሳሌም"፣ "ትዝታ"፣ "አንቺ ባለድሪ" እና "አየር ኃይላችን" የሚሉት ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ እነዚህ ዜማዎች ዛሬም ተወዳጅነታቸው የማይደበዝዝ ድንቅ የጥበብ ሥራዎቿ ናቸው።

በኪነ ጥበብ ህይወቷ በርካታ አይረሴ ድንቅ ስራዎችን ለህዝብ በማበርከት ታላቅ ባለውለታ የነበረችው አርቲስቷ፤ የሁለት ወንድና የአራት ሴት ልጆች እናት ነበረች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም