ቀጥታ፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎችን የእቅድ አፈጻጸም መርምሮ አጸደቀ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018 (ኢዜአ)፦የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎችን የእቅድ አፈጻጸም መርምሮ አጽድቋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በጠዋት ውሎው፤ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ እንዲሁም የሕገ-መንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻጸም ክትትል ቋሚ ኮሚቴዎችን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መርምሮና ተወያይቶ አጽድቋል።


 

የምክር ቤቱ አባላት ቋሚ ኮሚቴዎቹ ባቀረቡት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን፣ የኮሚቴዎቹ አመራሮችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የቀረቡት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲጸድቁ ለድምፅ ያቀረቡ ሲሆን፣ ምክር ቤቱም በሙሉ ድምፅ አጽድቋቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም