ቀጥታ፡

ፖርቹጋል ከስፔን : ተጠባቂው የጥሎ ማለፍ ፍልሚያ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)- 23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ የሚገቡ ሀገራት የሚለዩባቸው ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

ምሽት አራት ሰዓት ፖርቹጋል ከስፔን በዳላስ ስታዲየም  የሚያደርጉት ጨዋታ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ ስቧል።

ፖርቹጋል 32 የጥሎ ማለፍ ዙር ክሮሺያን 2 1 ስታሸንፍ ስፔን በበኩሏ ኦስትሪያን በመርታት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅላለች።

የአውሮፓ እግር ኳስ ኃያላኑ በዓለም ዋንጫው ሲገናኙ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ .. 2010 ባዘጋጀችው 19ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በተመሳሳይ 16 ውስጥ ተገናኝተው ስፔን በዴቪድ ቪያ ጎል 1 0 ማሸነፏ ይታወሳል

በወቅቱ ስፔን የዓለም ዋንጫው ባለቤት መሆን የቻለች ሲሆን፣ ይህ ስኬትም እስካሁን ድረስ በታሪኳ ያስመዘገበችው ብቸኛ የዓለም ዋንጫ ድሏ ነው።

በሩሲያ .. 2018 በተካሄደው 21ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በምድብ ሁለት ተገናኝተው ሶስት አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። 

ብሔራዊ ቡድኖቹ ከዚህ ቀደም እርስ በእርስ ባደረጓቸው 41 ጨዋታዎች ስፔን 17 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ስትይዝ ፖርቹጋል ብስድስቱ ድል ሲቀናት በቀሪ 18 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

በዛሬው ጨዋታ 41 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና 18 ዓመቱ ላሚን ያማል የሚጠበቁ ሲሆን በጨዋታው ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በሩብ ፍጻሜው ከአሜሪካ እና ቤልጂየም አሸናፊ ጋር ይገናኛል።


 

አሜሪካ ከቤልጂየም ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት በሲያትል ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ

ከዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አሜሪካ 32 ጥሎ ማለፍ ቦሲኒያ ሄርዞጎቪናን 2 0 ማሸነፏ እንዲሁም ተጋጣሚዋ ቤልጂየም በበኩሏ ሴኔጋልን 2 0 መመራት ተነስታ ውጤቱን ቀልብሳ 3 2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር መቀላቀሏ ይታወቃል።

ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም በዓለም ዋንጫው ሁለት ጊዜ ተገናኝተዋል።

ኡራጓይ .. 1930 ባዘጋጀችው የመጀመሪያ የፊፋ የዓለም ዋንጫ በምድብ አራት ተገናኝተው አሜሪካ 3 0 አሸንፋለች።

በርት ፓቴናውድ ሶስቱንን ግቦች ከመረብ በማሳረፍ በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ሀትሪክ የሰራ ተጫዋች መሆንም ችሏል።

ብራዚል .. 2014 ባዘጋጀችው 20ኛው ፊፋ ዓለም ዋንጫ 16 ውስጥ ተገናኝተው ቤልጂየም 2 1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ አልፋለች።

ኬቨን ብሮይን እና ሮሜሎ ሉካኩ ግቦቹን ሲያስቆጥሩ ሁለቱም ተጫዋቾች በአሁኑ የዓለም ዋንጫ የቤልጂየም ስብስብ ውስጥ ይገኛሉ።

ጁሊያን ግሪን በወቅቱ የአሜሪካን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ነው።

ሁለቱ ሀገራት 12 ዓመታት በኋላ በድጋሚ 16 ውስጥ ተገናኝተዋል።

በአጠቃላይ ሀገራቱ እርስ በእርሳቸው ሰባት ጊዜ ተጫውተው ቤልጂየም ስድስቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ስትይዝ በቀሪው አንድ ጨዋታ (በመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ) አሜሪካ ድል ቀንቷታል።

በአሜሪካ በኩል በውድድሩ ሶስት ግቦችን ያስቆጠረው የአሜሪካው ፍሎሪያን ባሎጉን ከቦሲኒያ ጋር በነበረው ጨዋታ የተመለከተው ቀይ ካርድ አግባብ ባለመሆኑ ምክንያት ተነስቶለት በጨዋታው ላይ እንዲጫወት መወሰኑን ፊፋ አስታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋኒቲኖ የቀይ ካርድ ውሳኔው በድጋሚ እንዲታይ ደውለው መጠየቃቸውን ተከትሎ ቀይ ካርዱ መነሳቱ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ላይ የተአማኒነት ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል።

ተጋጣሚዋ ቤልጂየም ውሳኔውን ፍጹም ተቀባይነት የለውም ስትል የተቃወመች ሲሆን የሁሉም ተሳታፊ ሀገራት መብት እንዲጠበቅና በእግር ኳሱ ፍትሃዊነት እንዲሰፍን ሁሉንም አማራጮች እንደምትመለከት አስታውቃለች።

ትራምፕ ውሳኔውን ተከትሎ ፊፋን ያመሰገኑ ሲሆን ፍትሃዊነትን ያሰፈነ ውሳኔ ሲሉ መግለጻቸውን ተከትሎ
ውሳኔው ከጨዋታው በፊት ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ለቤልጂየም በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በዓለም ዋንጫው ያስቆጠሩት ሊአንድሮ ትሮሳርድ እና ሮሜሎ ሉካኩ በጨዋታው የሚጠበቁ ተጫዋቾች ናቸው።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን
ጨዋታው አሸናፊዎች በሩብ ፍጻሜው ይገናኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም