ቀጥታ፡

ኖርዌይ እና እንግሊዝ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የ16ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር እንግሊዝ እና ኖርዌይ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅለዋል።

ቀደም ብሎ በተደረገው ጨዋታ ኖርዌይ ብራዚልን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ማምሻውን በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ በ79ኛው እና ደቂቃ 90ኛው ደቂቃ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የ25 ዓመቱ ሃላንድ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ሰባት አድርሷል።

ከአርጀንቲናው ሊዮኔል ሜሲ እና ከፈረንሳዊው ኪሊያን ምባፔ ጋር ተመሳሳይ የግብ መጠን ማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በጋራ መምራት ችሏል።

ለሀገሩ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 62 ከፍ አድርጓል።

ኔይማር በ100ኛው ደቂቃ የብራዚልን ብቸኛ ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።


 

በሌላ በኩል እንግሊዝ አዘጋጇን ሜክሲኮን 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅላለች።በአስር ተጫዋች ሁለተኛውን አጋማሽ የተጫወቱት እንግሊዞች በሀሪ ኬን እና ቤሊንግሀም ሁለት ጎሎች አሸንፈዋል።

ሀሪ ኬን በውድድሩ ስድስተኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ሀሪ ኬን በአለም ዋንጫው በድምሩ ያስቆጠራቸውን የጎሎች መጠን ወደ 14 ከፍ አድርጓል።

ኖርዌይ በቀጣይ ዙር እንግሊዝን በሚያሚ ትገጥማለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም