ቀጥታ፡

የሐረሪ ባህልና ስፖርት ፌስቲቫል በአሜሪካዋ ሜምፊስ ከተማ እውቅና አገኘ

​አዲስ አበባ፤ሰኔ 28/ 2018(ኢዜአ):-በአሜሪካዋ ሜምፊስ ከተማ የሐረሪ ባህልና ስፖርት ፌስቲቫል የከተማዋ በዓል ሆኖ እንዲከበር የከተማው ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ ወስኗል።

በከተማው የሀረሪ ማህበረሰብ በየአመቱ የሚያከብሩት የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል አከባበር እውቅና ማግኘቱ ባህሎቻቸውን፣ታሪኮቻቸውንና እሴቶቻቸውን ለሌላው ማህበረሰብ በላቀ ደረጃ ለማስተዋወቅ እንደሚያስችል ተጠቅሷል።

​እውቅናው ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ አለማት ለሚገኙ የሐረሪ ማህበረሰብ ትልቅ ኩራት ከመሆኑ ባሻገር የጥንታዊ ባህሎቻቸውን ጠብቆ ለማቆየትና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ መነሳሳትን የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።


 

የከተማዋ ምክር ቤት የሰጠው እውቅናም ከተማዋ ለባህል ብዝሃነት፣ለህዝቦች የእርስ በእርስ ትውውቅና ትስስር እንዲጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ተመላክቷል።

እንዲሁም በሜምፊስና በሐረር ከተሞች መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተጠቁሟል። በዓሉም በየአመቱ July 1 ቀን እንዲከበር ምክር ቤት በአዋጅ ደንጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም