ከንቲባ አዳነች አቤቤ 30ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ 30ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 28 2018(ኢዜአ) ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 30ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ ከተማ አስተዳደሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍ የምገባ ማዕከላት ግንባታ ላይ በትኩረት እየሠራ ይገኛል።
አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ሕይወት ለመለወጥና ለኑሮ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር በርካታ ሰው-ተኮር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ወቅታዊ ችግሮቻችንን በጋራ እየተሻገርን ብልፅግናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።
የማዕከሉ ተጠቃሚዎችን ሕይወት በዘላቂነት ለማሻሻል ከምገባ አገልግሎቱ ባሻገር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት እየተሠራ እንዳለ ጠቅሰዋል።
ዛሬ የተመረቀው 30ኛው የምገባ ማዕከል በርካታ አቅመ-ደካሞችን፣ አረጋውያንንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች በመደገፍ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ማዕከሉ እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ባለሀብቶችና አጋር አካላት ምስጋና አቅርበዋል።