ህዝቡ አሉታዊ የሆኑ የውስጥ እና የውጭ ተጽዕኖዎች ሳይበግሩት በምርጫው ያሳየው ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው-የጋራ ምክር ቤቱ - ኢዜአ አማርኛ
ህዝቡ አሉታዊ የሆኑ የውስጥ እና የውጭ ተጽዕኖዎች ሳይበግሩት በምርጫው ያሳየው ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው-የጋራ ምክር ቤቱ
አዲስ አበባ፤ሰኔ 28/ 2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ህዝብ አሉታዊ የሆኑ የውስጥ እና የውጭ ተጽዕኖዎች ሳይበግሩት በምርጫው ያሳየው ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ገለፁ።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደትን አስመልክቶ ውይይት አድርጓል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ስለሚወስዱት ትምህርትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ይገኙበታል።
እንዲሁም የሂደቱ ተዓማኒነት እና አካታችነትን በተመለከተ በቀጣይ ምን መደረግ እንዳለበት እና በጋራ መፍትሄዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል ብለዋል።
የጉባኤው ተሳታፊዎችም ህዝቡ አሉታዊ የሆኑ የውስጥ እና የውጭ ተጽእኖዎች ሳይበግሩት ያሳየው ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን አቶ ሰለሞን አየለ ለኢዜአ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።
ለዚህም ስኬት የበኩላቸውን ሃላፊነት ለተወጡ የፀጥታና የደህንነት አካላት፤ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የጋራ ምክር ቤቶች አመራሮች እና ሌሎች አካላት የጋራ ምክር ቤቱ ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።