ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱም የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ፣ የሜካናይዝድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ከፍያለው አምዴ፣ በመከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የዩንቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ ተገኝተዋል።


 

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ፣ የሠራዊቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች፣ ተጋባዥ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ታድመዋል።


 

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ምሩቃንም በኢንጅነሪንግ፣ ጤና ሣይንስ፣ ቢዝነስ፣ ማህበራዊ ጥናትና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም