ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብር የተገነባውን የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት መረቁ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2018 (ኢዜአ)፦‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብር የተገነባውን የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት መርቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‎ዛሬ ያስመረቅነው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት የ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብራችን ያፈራው ሌላኛው ታላቅ ስኬት ነው ብለዋል።


 

ይህ ዘመናዊ ሪዞርት ከ1,300 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ የስብሰባ አዳራሽና በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንትን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሪዞርቱ ከመዲናችን ባሻገር የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረግ ርዕያችንን ያጠናክራል፤ ለአካባቢው ማኅበረሰብም ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል ሲሉ ገልጸዋል።




‎መላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ዳያስፖራውና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይህንን አዲስ የሀገራችንን ዕንቁ ስፍራ በመጎብኘትና በመጠቀም፣ የኢትዮጵያን አዲስ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ምዕራፍ በጋራ እንድንቋደስ በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም