ቀጥታ፡

ኮሎምቢያ 16ቱን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የ32ቱ የጥሎ የመጨረሻ ማለፍ መርሐ ግብር ኮሎምቢያ ጋናን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማለዳ ላይ ተጠናቀቀው እና በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆን አሪያስ በ14ኛው ደቂቃ ጎሏን አስቆጥሯል።

ኮሎምቢያ ከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ ነበራት።

ጋና በጨዋታው አንድም ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ አላደረገችም።

ውጤቱን ተከትሎ ኮሎምቢያ 16 ውስጥ የገባች የመጨረሻ ሀገር ሆናለች።

የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር በቀጣዩ ዙር ከስዊዘርላንድ ጋር ትጫወታለች።

ጋና በ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር የተሰናበተች ሰባተኛ ሀገር ሆናለች።

የምዕራብ አፍሪካዋ ሀገር ከ18ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ህልሟ አልተሳካም።

ከአፍሪካ 16 ውስጥ መግባት የቻሉት ሞሮኮ እና ግብጽ ብቻ ናቸው።

ጨዋታውን ተከትሎ የ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የ16ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም