ቀጥታ፡

ግብጽ 16ቱን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ግብጽን አውስትራሊያን  በመለያ ምት አሸንፋለች።

ትናንት ማምሻውን በዳላስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢማም አሹር በ13ኛው ደቂቃ ግብጽን መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል።

የ28 ዓመቱ አሹር በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ያገባቸውን ጎሎች ብዛት ሁለት አድርሷል።


የግብጹ ተከላካይ መሐመድ ሃኒ በ55ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ጎል አውስትራሊያን አቻ አድርጓል።

ሃኒ በአንድ የዓለም ዋንጫ ሁለት ጎሎች በራሱ ላይ ያስቆጠረ የመጀመሪያ ተጫዋች ሆኗል።

ጨዋታው በመደበኛው ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ምክንያት 30 ደቂቃ የተጨመረ ሲሆን ጎል ሊቆጠር አልቻለም።

ግብጽ በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅላለች።


የሰሜን አፍሪካዋ ሀገር በዓለም ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስታሸንፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ሞሮኮን ተከትላ ወደ ቀጣዩ ዙር የገባች ሁለተኛ የአፍሪካ ሀገር ሆናለች።

ግብጽ በቀጣዩ ዙር ከአርጀንቲና ጋር ትጫወታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም