መቻል በሊጉ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
መቻል በሊጉ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ38ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል እና ሀድያ ሆሳዕና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አከናውነዋል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ57 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የውድድር ዓመቱን አጠናቋል።
ሀድያ ሆሳዕና በ48 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን ጨርሷል።
ዛሬ በተደረጉ የ38ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህር ዳር ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በወላይታ ድቻ እና በኢትዮጵያ ቡና መካከል የተደረገው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በሃዋሳ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።