የአስተዳደሩ ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ተግባራት በተቀናጀ መንገድ ድጋፍና ክትትል በማድረጉ ውጤት ተገኝቷል - ኢዜአ አማርኛ
የአስተዳደሩ ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ተግባራት በተቀናጀ መንገድ ድጋፍና ክትትል በማድረጉ ውጤት ተገኝቷል
ድሬደዋ፤ ሰኔ 26/2018(ኢዜአ)፦) የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የአስፈጻሚውን አካላት ተግባራት በተቀናጀ መንገድ ድጋፍና ክትትል በማድረጉ ውጤት መገኘቱን የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈጉባኤ አብዲ ሙክታር ገለጹ።
ምክር ቤቱ የስራ ዘመኑን መደበኛ ጉባኤ የፊታችን ሰኞ ያካሂዳል።
የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታር፣ ምክር ቤቱ የአስፈፃሚውን አካላት የአምስት አመታት የስራ እቅድና አፈጻጸም የክትትልና የድጋፍ ስራዎችን አስመልክተው ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ምክር ቤቱ በቋሚ ኮሚቴዎቹና በሚቀርቡ ሪፖርቶች የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ውጤታማ ስራዎች እንዲከናወኑ አድርጓል ብለዋል።
በሌላ በኩል የፍርድ ቤቶችን የአደረጃጀት፣ የበጀት እና በዳኞች ሹመት ላይ ቁጥጥር በማድረግም ለፍትህ ስርአቱ ስኬት የበኩሉን መወጣቱን አንስተዋል።
ምክር ቤቱ አስፈጻሚው አካል የህዝብን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የወጡ ህጎችና ደንቦች ከህገ መንግስቱ ጋር በተናበበ መልኩ ስራ ላይ መዋሉን ሲከታተል መቆየቱን አንስተዋል።
የኢኮኖሚ ዘርፎች በተቀናጀ መንገድ እንዲተገበሩ ድጋፍ በማድረግም ለውጤቱም የድርሻውን ማበርከቱን አንስተዋል።
በመጪው ሰኞ በሚካሄደው በ3ኛው የስራ ዘመን 5ኛው አመት 12ኛው መደበኛ ጉባኤውም የአስፈጻሚውንና የምክር ቤቱ ተጠሪ ተቋማትን የ2018 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ይገመግማል ብለዋል።
በተጨማሪ የ2019 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።