ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 38ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄዷል።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ51 ነጥብ ከነበረበት ሰባተኛ ደረጃ ወደ ስድስተኛ ከፍ ብሏል።

ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ 51 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም