የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ‘Connectivity Award’ ሽልማት አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ‘Connectivity Award’ ሽልማት አገኘ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የአቪዬሽን እና ቱሪዝም ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የ‘Connectivity Award’ ሽልማት ማግኘቱን አስታወቀ።
ሽልማቱን ያገኘው ከኤር ትራንስፖርት ኒውስ መሆኑን አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።
ሽልማቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ውስጥ ለዘረጋው የአየር ትሥሥር እና አብሮ የመሥራት ጥምረቶች ዕውቅና ለመስጠት ያለመ መሆኑም አየር መንገዱ አመልክቷል።