ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህር ዳር ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ38ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህር ዳር ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ከረፋድ በኋላ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዩጋንዳዊው ሳይመን ፒተር እና ናትናኤል ዳንኤል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አደም አባስ የባህር ዳር ከተማን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ47 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል።

ተጋጣሚው ባህር ዳር ከተማ በበኩሉ በ48 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

ባህር ዳር ከተማ በሊጉ በበርካታ ጨዋታዎች (21 ጊዜ) አቻ በመውጣት ዓመቱን አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አጥቂ ናትናኤል ዳንኤል በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ 15 በማድረስ፣ እኩል ግብ ካለው የፋሲል ከነማው ታምራት እያሱ ጋር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ደረጃ በጋራ መምራት ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም