ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 38ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን መርሐ ግብር

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ38ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬም ቀጥሎ ሲውል፣ ሶስት ጨዋታዎች ይስተናገዳሉ።

መቻል ከሀድያ ሆሳዕና ከቀኑ 10 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ከ37 ጨዋታዎች 56 ነጥብ የሰበሰበው መቻል በ56 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ሀድያ ሆሳዕና በበኩሉ በ47 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በ37ኛ ሳምንት በሸገር ከተማ 2 ለ 0 የተሸነፈው መቻል ዓመቱን በድል ለማጠናቀቅ ይጫወታል።

መቻል ካሸነፈ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን ያጠናቅቃል።

ሀድያ ሆሳዕና በሊጉ  በ37ኛ ሳምንት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር አንድ አቻ በመውጣት በሊጉ መቆየቱን ማረጋገጡ የሚታወስ ነው።

ሌላኛው መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያገናኛል።

ወላይታ ድቻ በ50 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ቡና በ50 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በ37ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ አዳማ ከተማን 2 ለ 0፣ ኢትዮጵያ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን 3 ለ 0 አሸንፈዋል።
ሁለቱ ቡድኖች ዓመቱን በድል ለማጠናቀቅ ይጫወታሉ።

ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባህር ዳር ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ46 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ባህር ዳር ከተማ በበኩሉ በ47 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ከድል የራቀው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓመቱን በድል ለመቋጨት ይፋለማል።

ተጋጣሚው ባህር ዳር ከተማ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ አላገኘም። ቡድኑ ዓመቱን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ ይጫወታል።

ባህር ዳር ከተማ በሊጉ በበርካታ ጨዋታዎች (20) አቻ የወጣ ቡድን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም