ስዊዘርላንድ አልጄሪያን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች - ኢዜአ አማርኛ
ስዊዘርላንድ አልጄሪያን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ስዊዘርላንድ አልጄሪያን 2 ለ 0 አሸንፋለች።
ማለዳ ላይ በቢሲ ፕሌስ ቫንኩቨር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሬል ኢምቦሎ እና ዳን ንዶይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አልጄሪያ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት ብትወስድም ጎል ማስቆጠር አልቻለችም።
ስዊዘርላንድ ያገኘቻቸውን የግብ እድሎች በሚገባ መጠቀሟ አሸናፊ አድርጓታል።
ግብ ያስቆጠረው ብሬል ኢምቦሎ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
ውጤቱን ተከትሎ ስዊዘርላንድ ከ88 ዓመታት በኋላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በማሸነፍ 16 ውስጥ ገብታለች።
ስዊዘርላንድ በቀጣዩ ዙር ከጋና እና ኮሎምቢያ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
አልጄሪያ በጥሎ ማለፉ የተሰናበተች ስድስተኛ የአፍሪካ ሀገር ሆናለች።