የዜጎችን አኗኗር ምቹ እና ዘመናዊ ማድረግ የኮሪደር ልማት መርሃ-ግብራችን ዋነኛ ግብ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የዜጎችን አኗኗር ምቹ እና ዘመናዊ ማድረግ የኮሪደር ልማት መርሃ-ግብራችን ዋነኛ ግብ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ ፤ሰኔ 26/2018 (ኢዜአ)፦የዜጎችን አኗኗር ምቹ እና ዘመናዊ ማድረግ የኮሪደር ልማት መርሃ-ግብራችን ዋነኛ ግብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ያየነው የአርባ ምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፤ ዘመናዊ የአስፋልት መንገድ እና መብራቶችን እና ዲጂታል ስክሪኖችን ያካተተ ሲሆን በተጠናቀቁት የኮሪደር ስራዎች ላይ አገልግሎቱ ተጀምሯል ብለዋል።
ጥራቱን የጠበቀ ዘመናዊ መሠረተ-ልማትን ከአረንጓዴ ልማት ጋር በማስተሳሰር የከተሞቻችንን ምቹነት የማረጋገጥ ስራችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
በመሆኑም የዜጎችን አኗኗር ምቹ እና ዘመናዊ ማድረግ የኮሪደር ልማት መርሃ-ግብራችን ዋነኛ ግብ ነው ያሉት።