ቀጥታ፡

የሀገር ውስጥ ምርትን በራስ አቅም ማሳደግ የሉዓላዊነታችን መሰረት ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ)፡- የሀገር ውስጥ ምርትን በራስ አቅም ማሳደግ የኢኮኖሚ ነጻነታችን እና የሉዓላዊነታችን መሰረት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በጋሞ ዞን የሚገኘውን እና ነሐሴ 2017 ዓ.ም ላይ ሥራ የጀመረውን 'ዮ ሆልዲንግ’ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ መጎብኘታቸውን አስታውቀዋል።


 

ፋብሪካው የኢንዱስትሪዎቻችንን ፍላጎት በሀገር ውስጥ በመተካት ከውጭ የሚገባ ምርትን ያስቀረ መሆኑን ገልጸዋል።

ለአካባቢው ነዋሪዎችም የሥራ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል በመልዕክታቸው።


 

የሀገር ውስጥ ምርትን በራስ አቅም ማሳደግ የኢኮኖሚ ነጻነታችን እና የሉዓላዊነታችን መሰረት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።

‎የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት በጠንካራ ስራ በሀገር ውስጥ በማልማት የኢኮኖሚ ልዕልናችንን የምናረጋግጥበት ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም