ቀጥታ፡

በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ):-በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የዝናብ ሁኔታ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ይሄዳል።

በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ በብዙ ስፍራዎች የሚሸፍን ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የዝናብ ሁኔታ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ይሄዳል ብሏል።

ከሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ጋር ተያይዞ በሚቀጥሉት አስር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የዝናብ ሁኔታ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ይሄዳል።

በዚህም ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከባድ መጠን ዝናብ እንደሚኖራቸው ገልጿል።

በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በአካባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት በ24 ሰዓት ውስጥ እስከ 30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ነጎድጓዳማና በረዶ አዘል ዝናብ እንደሚኖርና ጥንካሬውም ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ የሚዘንብበት ወር መሆኑን አንስቷል።

በሚቀጥሉት አስር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ብሏል።

በተጨማሪም ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር፣ በምስራቅ አማራ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ጠቁሟል።

በመኸር ሰብል አብቃይ በሆኑት አካባቢዎች የሚኖረውን መልካም አጋጣሚን መጠቀም እንደሚያስፈልግና አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ጥንቃቄዎችን መውሰድ ያስፈልጋል ብሏል።

ይህም የአፈር ውስጥ እርጥበትን የሚያሻሻል ከመሆኑ አንጻር ዘር ለመዝራት፣ አስቀድመው ለተዘሩና በተለያዩ እድገት ደረጃ ላይ ላሉ ሰብሎች፣ ለቋሚ ተክሎችና የጓሮ አትክልቶች አዎንታዊ ፋይዳ እንዳለው ጠቁሟል።

የገጸ ምድር የውሃ ሽፋን በአብዛኛው ተከዜ፣ መረብ፣ አባይ፣ ባሮ አኮቦ፣ የላይኛው እና መካከለኛ ኦሞ ጊቤ፣ ስምጥ ሸለቆ እና የአዋሽ ተፋሰሶች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል።

በላይኛው እና መካከለኛው ገናሌ ደዋ፣ ዋቤ ሸበሌ እንዲሁም በኦጋዴን ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ መካከለኛ የሚደርስ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል።

ከፍተኛ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት በሚጠበቅባቸውና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ የጎርፍ ክስተት፣ የመሬት መንሸራተት እና የወንዞች ሙላት ሊያስከትል ስለሚችል ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ከወዲሁ መስራት ያስፈልጋል ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም