የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን አዲስ የመንገደኞች በረራ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን አዲስ የመንገደኞች በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/ 2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን አዲስ የመንገደኞች በረራ ጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ እንዲሁም የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በረራው የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጎለብት ነው።
በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ያለውን የንግድ፣ ቱሪዝም እና የባህል ልውውጥ የሚያሳድግ መሆኑንም ጠቁመዋል።
አየር መንገዱ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን የሚያደርገው በረራ በአውሮፓ 23ኛ መዳረሻው መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ በበኩላቸው፤ አየር መንገዱ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን ያስጀመረው በረራ የሀገራቱን የንግድና ቱሪዝም ግንኙነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል።
ሊዮን የፈረንሳይ ሁለተኛዋ የኢኮኖሚ ማእከል መሆኗን ጠቅሰዋል።