ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ቀን መርሐ ግብር የቀን ለውጥ ተደረገባቸው


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/ 2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ቀን መርሐ ግብር በዝናብ ምክንያት የመካሄጃ ቀናቸው ተራዝሟል።

የሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት ነበር።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ቅዳሜ ሰኔ 27 አዲስ አበባ ላይ ሊያከናውን የነበረውን የሲዳማ ቡና እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ የ2018 ዓ.ም የሊጉ የመዝጊያ መርሐ ግብር በዝናብ ስጋት ምክንያት ወደ ሃዋሳ ከተማ በማዘዋወር እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያከናውን ዛሬ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም የተፋላሚ ክለቦች ዝቅተኛ 72 ሰዓት እረፍት እንዲያገኙ በማሰብ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ አምስት ሰዓት እንዲደረግ መወሰኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መካከል የሚደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት በሳተላይት እና ኦንላይን አማራጮች እንደሚተላለፍም አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም