ቀጥታ፡

በክልሉ ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ  ፈተና ስኬታማነት ዝግጅት ተደርጓል

ጋምቤላ ፤ ሰኔ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ስኬታማ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል። 

የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡኩኝ ኦኬሎ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ስኬታማነት ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ በዛሬው ዕለት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ በስኬት ተጀምሯል።


 

በክልሉ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 8 ሺህ 536 የተፈጥሮና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን በበይነመረብና በወረቀት ለማስፈተን ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ከተፈታኞቹ መካከል 1 ሺህ 448 ተማሪዎች በበይነመረብ (ኦንላይን) በስድስት ዙር እንደሚፈተኑ ጠቁመው፤ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ፈተናውን እየወሰዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በበይነመረብ (ኦንላይን) የሚሰጠው ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ በጋምቤላ ከተማ ኤልያና ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው፤ የወረቀት ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን የሚወስዱት በጋምቤላና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም