ቀጥታ፡

ሞሮኮ ኔዘርላንድስን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የ32 ዙር ጥሎ ማለፍ ተጠባቂ መርሐ ግብር ሞሮኮ ኔዘርላንድስን በመለያ ምት አሸንፋለች።

ማለዳ ላይ በተጠናቀቀው እና በሞንቴሬይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኮዲ ጋፕኮ በ72ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

የጋፕኮ ጎል በፈጣን የማጥቃት ሽግግር የተገኘ ሲሆን ክሬሴንሲዮ ሳመርቪል ለግቧ መቆጠር ምክንያት ሆኗል።

ከግቡ መቆጠር በኋላ በቅርቡ በእርግዝና ወቅት ሁለተኛ ልጁን በሞት ያጣው ጋፕኮ ስሜቱን በማልቀስ ገልጿል።

የ27 ዓመቱ ጋፕኮ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ሶስት አድርሷል። በአጠቃላይ በውድድሩ ስድስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ጨዋታው በኔዘርላንድስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ሲባል ኢሳ ዲዮፕ በ91ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ያስቆጠረው ጎል ሞሮኮን አቻ አድርጓል።




መደበኛው 90 ደቂቃ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ምክንያት 30 ደቂቃ ተጨምሯል።

በጭማሪ ሰዓት ግብ ባለመቆጠሩ ምክንያት ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።

በዚህም ሞሮኮ በመለያ ምት 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ጥሎ ማለፍ ገብታለች።

ሞሮኮ በጨዋታው በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎችን በመፍጠር ተሽላ ተገኝታለች።

ጨዋታው በታክቲክ የታጠረ ነበር ማለት ይቻላል።

ውጤቱን ተከትሎ ሞሮኮ ወደ 16 ውስጥ ገብታለች። በቀጣዩ ዙር ከካናዳ ጋር ትገናኛለች።

ሞሮኮ በ22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያ የአፍሪካ ሀገር መሆኗ የሚታወስ ነው።

ኔዘርላንድስ የዓለም ዋንጫ ጉዞዋ 32 ውስጥ አብቅቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም