ቀጥታ፡

ጀርመን ከዓለም ዋንጫው ተሰናበተች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የ32 ዙር ጥሎ ማለፍ ፓራጓይ ጀርመንን በመለያ ምት አሸንፋለች።

ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቦስተን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጁሊዮ ኢንሲሶ በ42ኛው ደቂቃ ፓራጓይን መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል።

ካይ ሃቫርትዝ በ54ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ጀርመንን አቻ አድርጓል።

ጨዋታው በመደበኛ ክፍለ ጊዜ በመጠናቀቁ ምክንያት 30 ደቂቃ ተጨምሯል።

በጭማሪ ሰዓትም ግብ ባለመቆጠሩ ምክንያት ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።

ፓራጓይ በመለያ ምት 4 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች።

የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ፓራጓይ 16 ውስጥ ከፈረንሳይ እና ስዊድን አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።

የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን ሳይጠበቅ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም