ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 22/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም፤ በኢኮኖሚያዊ ትሥሥር፣ በሰላምና ደኅንነት እንዲሁም በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ሀገራቱ የሚጋሩት ከድንበር ያለፈ ሕዝቦቻቸውንና መፃዒ መዳረሻቸውን ጭምር መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም