ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በረቂቅ በጀቱ ላይ መወያየትን ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በረቂቅ በጀቱ ላይ መወያየትን ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፤ሰኔ 22/2018 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 29ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያደርጋል።
ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር እንደሚወያይ ገልጿል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ሦስት ረቂቅ አዋጆችን ማለትም የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ እና የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርባቸውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቦች መርምሮ አዋጆቹን ያፀጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።